ሞመንተም (ህብረምጥቀት) ለኢትዮጵያ በመቋቋም ላይ ያለ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው:: የድርጅቱ ዋና ዓላማ ትውልዱ አዕምሮውን በምልአት በማበልጸግና መተማመንን በማዳበር የበለጸገች ኢትዮጵያን በቶሎ እንዲፈጥር መርዳት ነው::
ዓርብ 11 ዲሴምበር 2015
ማክሰኞ 8 ዲሴምበር 2015
ሰኞ 7 ዲሴምበር 2015
Ethio-Sudan Boarder dispute and my personal view ( in Amharic)
የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ፣ ምነው ጩኽት በዛ? ከመንግስት ግልጽ
መግለጫ ይሰጠን
መግለጫ ይሰጠን
ሰሞኑን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ስለ ኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ እጅግ ብዙ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው:: ለምሳሌም የሚከተሉትን መጎብኘት ይቻላል::
“እሪ በየጎራው በየሸንተረሩ
እሪ ካልተባለ አይረዳም ሀገሩ”
ውድ ኢትዮጵያውያን እናወዳጆቻችን፣
የሀገራችን ህዝብ ካቅሙ በላይ የሆነ ነገር በመጣበት ጊዜ “የሀገር ያለህ፣ የመንግስት ያለህ፣ የህግ ያለህ ድረሱልኝ” እያለ መጮህ የተለመደ ነው:: ያንንም የቆየ ባህላዊ የችግር ማሰሚያ እና መፍትሄ ማግኛ ዘዴ ለማጽናት እንዲህ የሚል ግጥም ይዜማል፣ “እሪ በየጎራው በየሸንተረሩ እሪ ካልተባለ አይረዳም ሀገሩ” ይባላል:: አብዝቶ ለሚጮህ ሰው ቢዘገይ እንኳ የሚረዳው አያጣም:: ሊረዳ የመጣም ወገን በቆየው ሀገራዊ ባህልና ወግ መሰረት ለተበደለው ሰው እልባት ሳይሰጥ ወደ ቤቱ አይገባም:: በደል ሳያወጣ የገባ፣ እሪታ ሰምቶ ቤቱ የተቀመጠ ሰው “ጥቁር ውሻ ይውለድ” ተብሎ ሀገር በጥንት ስለተማማለ እና በዘመናችንም ቢሆን ለሪታ መልስ ያልሰጠ ከእድር እና ሌሎች ባህላዊ ክንውኖች ስለሚሰረዝ ህዝባችን መንግስት መድረስ ባልቻለበት አካባቢ በእሪታ ሰላሙን ሲያስከብር ኖሯል::
ዛሬ በእኛ ዘመን ተራራ ላይ ወጥቶ እሪ ማለት በተለይም በከተሜው ዘንድ የሚታሰብ አይደለም፣ እሪ ቢባልስ ማን ሲረዳ!:: የዘመናችን እሪታ በመረጃ መረብ ከሆነ ሰነባበተ:: በዚህች ሰዓት ይችን ጽሁፍ ለማካፈል ያስገደደኝም ጉዳይ እጅግ በጣም የበዛ ሀገራዊ እሪታ፣ ጩኽት በመበርከቱ ነው:: እንደግለሰብ የማንም ወገን ተቃዋሚ ወይንም ደጋፊ አይደለሁም፣ መሆንም አልፈልግም:: ነገር ግን ምንጊዜም፣ በህይወት እስከምቆይበት ዘመን ድረስ ከእውነት ጎን ለመቆም ለህሌናየ ቃል ገብቻለሁ:: እውነት ምንድነች? በምንስ ትታወቃለች? ብየም ራሴን መጠየቄ አልቀረም:: ሀሰት የሆነ ነገር ወሬው ቦግ እልም ይላል፣ ዛሬ ተሰምቶ ነገ ይጠፋል:: እውነት ከሆነ ግን እጅግ በጣም ተደጋግሞ ከመሰማቱም በላይ ለብዙ ጊዜ ይቆያል፣ ደጋፊዎቹም እየበዙ ይሄዳሉ:: ብቻ እውነትን ለማጣራት ለሚሞክር ሰው የራሷ የሆነ መታወቂያ ባህሪ አላት፣ እናም ከዚህ ተነስቸ ከባድ እውነት የመሰለኝን ነገር የበለጠ ለማወቅ ስለፈለኩ እና እውነትነቱም ስለከነከነኝ በውስጤ የተሰማኝን ብሶት ከወዳጆቸ ጋር ለመካፈል ወደድሁ::
ከምንም በላይ ውስጤን የነካኝ እና ሁላችንንም ይመለከተናል ብየ ያሰብኩት ነገር የሀገራችን የዳር ድንበር ጉዳይ ነው:: ባለፉት ዘመናት ሁሉ ህዝብ በማያውቀው ሁኔታ የተፈጸሙ የድንበር ውሎች በሙሉ ተግባራዊ እየሆኑ ሀገራችን ከባህር በሯ ተገልላ የበይ ተመልካች ከሆነች እነሆ 24 ዓመት አለፈ:: በዓለም እጅግ በጣም ትንሿ እና ደካማዋ ሀገር፣ 570, 000 (አምስት መቶ ሰባ
ሺህ ) ህዝብ ብቻ ያላት ጅቡቲ የባህር በር ባለቤት ስትሆን ከ100,000,000 (ከ 1መቶ ሚሊየን ) ህዝብ በላይ ያላት ታላቂቷ ሀገራችን ወደብ አልባ ሆነች:: ከ2000 ኪሜ ርዝመት በላይ የሚሸፍን የባህር ጠረፍ እያለን ጣሊያን፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ግብጽ፣ ቱርክ እና ሌሎች የጥንት ጠላቶቻችን ባሴሩት ሴራ እና የእኛም መሪዎች ባጠፉት ጥፋት እነሆ ሙሉ በሙሉ ከቀይ ባህር ጠረፍ ከተገለልን 24 ዓመት አለፈን:: በቀን ከሶስት ሚሊየን ዶላር በላይ የወደብ ኪራይ እየከፈልን፣ እየተሳቀቅን፣ ጅቡቲን ቀን ሌት እያባበልን ለመኖር ግደታችን ሆነ:: በጦርነት የቆሰለው ህዝባችንም ህመሙ ስለጸናበት ይሁን እስኪ ቀን ይለፍ በማለት አንገቱን ደፍቶ ዝም አለ::

ጠላት ዝም ስለተባለ አይተውምና የባህር በራችንም ካጣን በኋላ ጦርነት አገርሽቶ ለባድሜ ቢያንስ 100, 000 (አንድ መቶ ሺህ)
ህዝብ ተገብሮ ያለፍሬ ጦርነቱ ተቋጨ:: ሁላችንም ለጦርነቱ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ገብረናል:: ዛሬ ደግሞ እንደገና ለዘመናት በሰላም ድንበራችን ተከብሮ በኖረበት በሱዳን በኩል 1600 ኪሜ (አንድ ሺህ ስድስት መቶ) ርዝመት ያለው መሬት ተቆርሶ ለሱዳን ሊሰጥ ስምምነት እየተካሄደ እንደሆነ መስማት ከጀመርን እነሆ ዓመታት ተቆጠሩ:: ነገሩ ስር መሰረት ላይኖረው ይችላል በማለት ህዝቡም ዝም ብሎ ሲጠብቅ ሰሞኑን የድርድሩ ሂደት ከ4 ቀን በፊት እንደተካሄደ እና በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን እጅግ ብዙ ሚድያዎች እየገለጹ ነው::

በአካል የምንገናኝ እና አብረን የምንኖር ሰዎች ግን ትንታፍሽ ለማለት እንኳ ሁሉም በፍርሀት ስለተያዘ በሆዱ ይብሰለሰላል:: ዞሮ ዞሮ የተደገሰ መከራ ይዋል ይደር እንጂ መምጣቱ አይቀርም:: ስለዚህ ይህ ጉዳይ የሚመለከተው ሁላችንም ስለሆነ በሚቻለው ሁሉ እውነተኛ መረጃ ብንሰበሰብ እና የምናውቀውን ብንካፈል መልካም ነው:: ሀገራችን ለዚህ የደረሰችው በመንግስታት ብርታት እና በጎ ፈቃድ ብቻ ሳይሆን በህዝቧ ታላቅ መስዋእትነት ነው:: ዛሬም ህዝብ በሁኔታው ሊመክር ይገባል:: እሪታው በየቦታው በዝቷል፣ ለእሪታ መልስ መስጠት ደግሞ የኢትዮጵያ ባህልና ወግ ነው:: ሀሳቡን አውጥቶ የተናገረውን ሁሉ ዝም በል እያሉ ከማስፈራራት ይልቅ ስለተፈጠረው ነገር ህጋዊ እና ስርዓት ያለው ምላሽ መስጠት ዘመናዊነት ነው:: ከመንግስት እርግጠኛ የሆነ መግለጫ እና መልስ እንፈልጋለን:: በ21ኛው ክፍለ ዘመን እየኖርን ስለሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ለመጠየቅ እና ለመጻፍ የምንሳቀቅበት ነገር ማቆም አለበት:: ጥንትም ቢሆን ተጨቋኝ የነበሩ ዜጎች እና ሀገራት ነጻነታቸውን ያገኙት በመንግስታት በጎ ፈቃድ ሳይሆን ቆራጥ ግለሰቦች ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ነው::
የሚመለከታችሁ ባለስልጣናት እና የባለስልጣን ወገኖች ሆይ፣
ሁሉም ያልፋል፣ ዛሬ በደስታ የምትፈሱበት ቤታችሁ፣ ግቢያችሁ፣ ሀብታችሁ፣ የሚያስደስቱ ልጆቻችሁ፣ እናንተም ራሳችሁ፣ እኛም ድሆች ሁላችን ወዘተ ሁሉም ያልፋል:: ዓለም ጠዋት ታይቶ ረፋድ ላይ እንደሚረግፍ ጤዛ እንደሆነች ለሁላችንም ግልጽ ነው:: ይህ እየታወቀ በጊዜያዊ ስሜት በመታወር ታላላቅ ሀገራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ጉዳዮች እንደቀልድ ማሳለፍ ወይንም ተንኮል ያዘለ ነገር ለትውልድ ማውረስ ዘላለማዊ ሀፍረት ነው:: ግለሰብ ዘመኑ አጭር ይሁን እንጂ ትውልድ ይቀጥላል:: ለሚቀጥለው ትውልድ የመከራ እርሾ አስቀምጦ ማለፍ ደግሞ የታሪክ ህጸጽ መሆን ነው:: በዚህ በብርሀን ዘመን
የጨለማ ስራ በሀገራችን እንዳይሰራ የሚመለከተው ሁሉ በንቃት ሊጠብቅ ይገባል:: በዘመናችን መጠጣት ያለብንንም ጽዋ ለመቀበል መዘጋጀት ግድ ይላል:: ፈራንም አልፈራንም ሞት ያባት ርስት ስለሆነ በሁላችንም ላይ ይመጣል:: ከኖርን በፍቅርና በእውነት እንኑር፣ መሞት ካለብን ደግሞ ለሀገራችን እና ለተተኪው ትውልድ ጥቅም አስተዋጽኦ አበርክተን እንለፍ:: ከምንም በላይ የተደበቀውን እና የረቀቀውን ምስጢር የሚያውቅ አምላካችን፦

1) የቀደሙትን ሴረኞች ሁሉ ድብቅ ተንኮል እንዳከሸፈ ዛሬም በውስጣቸው ተንኮል ያዘሉ የቀበሮ ባህታዊ የሆኑ ጠላቶቻችን ሁሉ ያጋልጣል::
2 የፈርኦንን ጠንቋዮች ያሳፈረች እባቦችን በሙሉ ጠቅልላ የዋጠች፣ ነገር ግን ማንንም ሰው ያልበላች የሙሴ እባብ ዛሬ የተንኮልን ሴራ ትበላለች፣
ትእቢት ወጥሮት፣ በጉልበቱ ተመክቶ እስራኤልን ሲያንቀጠቅጥ የነበረውን ጎሊአድን በፍየል እረኛው በዳዊት ወንጪፍ ደፍቶ የጣለ እና ሰራዊቱን የበተነ የዳዊት አምላክ ዛሬ ያችን ኃይል ለሀገራችን ይልካል፣
በሰራዊታቸው ብዛት እና በመሳሪያ ጥራት ሲመኩ የነበሩትን ሁሉ ጠላቶቹን በትንሽ ነገር ድል ያደረገ የጌድዮን አምላክ ዛሬ ያችን ኃይል ለኢትዮጵያ ይልካል፣
እንግሊዝና ጣሊያን ተመካክረው ኢትዮጵያን ለማጥቃት በተነሱበት ዘመን በራሳቸው መሀል ጦር ቀስቅሶ የጣሊያንን
ሰራዊት በእንግሊዝ ያስጨረሰ እና ምክራቸውን ያፈረሰ አምላክ ዛሬም የኢትዮጵያን ጠላቶች ደባ ያፈርሳል፣
ኢትዮጵያ ሀገራችን ለብዙ ሺህ ዓመታት ሴራ ሲሴርባት የኖረች እና ሁሉንም ሴራዎች አክሽፋ ለዚህ የደረሰች ሀገረ እግዚአብሄር የየዋህና የጀግና ህዝብ ሀገር ነችና ዛሬ ቢሆን ሁሉንም በድል ትወጣለች::

ህዳር 27 ቀን፣ 2008 ዓ ም
A
a
ዓርብ 23 ኦክቶበር 2015
momentum for Ethiopia (ሕብረምጥቀት ለኢትዮጵያ): ሞመንተም ለኢትዮጵያ-መግቢያ
momentum for Ethiopia (ሕብረምጥቀት ለኢትዮጵያ): ሞመንተም ለኢትዮጵያ-መግቢያ: ሞመንተም ለኢትዮጵያ የለውጥ አፋጣኝ እና የገጽታ ግንባታ ማህበር ሀገር ሀገር ከፖለቲካ ቡድን፣ ከሃይማኖት ወይንም ከሌሎች የግል ጉዳዮች ሁሉ የበለጠ ዋጋ ያለው፣ የቀደሙ አባቶች እና እናቶች ተፈጥሮን አልምተ...
ሰኞ 19 ኦክቶበር 2015
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)